ግጥም ብቻ 📘
/getem

ግጥም ብቻ 📘

Open in Telegram  →

ai summary

This channel shares curated artistic works daily.

for whom: This channel is for individuals interested in appreciating and discovering diverse artistic creations.

64.2Ksubscribers
no data yetavg reach
11.6%ER
0.6posts/day

charts · trends

64.2K
0(0.00%)
Jul 2 – Jul 20 · 7

📨 Recent posts

35 total

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ° ብሸፍተም ሰው ስገድል.. ስትጠራኝ ሳትሸነግል.. ቀስቴን ጥዬ ተሸነፍኩኝ አንተን ሳይህ 'ረገፍኩኝ፨ ድንገት ራደ ሰዉነቴ፣ ተፈታልኝ ሰንሰለቴ፨ ° ለካ እንዲ ነህ ሰው ስትለውጥ ለካ እንዲ ነህ ሰው ስትጠራ፣ ጨካኙን ልብ ደግ ያልሰራ፣ ታኖራለህ ስታራራ፨፨ ° ለካ እንዲ ነህ ስታንኳኳ፣ ጻዲቅ ሆነ ገዳዩ እንኳ፨! By @alem3_b [ዓለም] @getem @getem @getem

5d ago👁 2.8Kopen

እንዳትረሺኝ ብዬሽ፤ አትርሳኝ ብለሽኝ ፤ በቃል ክር አስሬሽ፤ በቃል ክር አስረሽኝ፤ በደልሽኝ በደልኩሽ፤ በደልኩሽ በደልሽኝ ፤ ቃልሽን አከበርሽ ቃሌን አከበርኩኝ ፤ ይሄ በደላችን... እንኳን በ'ዚህ ሕይወት በመቃብርም ውስጥ ችሎ አያረሳሳም፤ ደግሞ እንደምታውቂው የወዳጅ ፍቅሩ እንጅ በደሉ አይረሳም ። By Tewodros kassa @topazionnn @topazionnn

7d ago👁 5Kopen

እውነትም ሰገነት! ውሸት አልነበረም ያ ሁሉ ሙገሳ፥ ሰማይ ታህል ነበር ጨረቃ አንችን ለብሳ። አድማስና ማማ ማጋነን ቢመስል፥ ወንዝ እንኳ ሚረጋው ሲቃኝ ባንቺ ምስል፤ እውነት? ያባይ ጅረት ሳቅሽን ይበልጣል? የጢሱ ርግብታ? ከርጋታሽ ይሰክናል? እስቲ ጽጌሬዳ?ይመ--ስልሻል ወይ፣ ይቅርና በበጋ እርሙንስ በጸደይ?! ንግግርሽ ሃገር አርምሞሽ አሃጉር አንቺ ላይ ከረመ ውበት ሲያንጎራጉር!። ሃሳብሽ ገራገር መርኅሽ ዝምታ፣፨ . . . እውነትም ሰገነት ፣ እውነትም ከፍታ !። 🙌🏿 By @alem3_b [ዓለም] @getem @getem @getem

8d ago👁 2.6Kopen

ድሮ አንቺን ለማየት ሰፈርሽ ስመጣ አንዲት ዝርግ ድንጋይ አየሁ ተቀምጣ ፤ ቁጭ አልኩኝ በድንገት እንዲህ እንደ ዘበት… ያፈቀረሸ ልቤ ፣ ሳሉ ሲነሳበት ማስታገሻ ነበር ፣ ሰፈርሽ መገኘት። ዛሬስ አትይኝም? እዛው ተቀምጬ አትመጣም ወይ? እያልሁ አንቺ ብትቀሪ… : ዲግሪ ጭኖ መጣ ሀይስኩል ተማሪ። እዛው ትናንትና እዛው አንቺ ሰፈር ከጠፍጣፉ ድንጋይ ሳልነሳ ቀንቶኝ… : ያምና ብላቴና ያልፈኛል ገላምጦኝ። አትገረሚም ወይ? ሳልነሳ ከዛ ቤተ መቅደስ ታዛ ከስር የማይጠፋ የወንጌል ሰባኪ ቅስናውን ገድፎ በየመሸታ ቤት ሲያወርድ ያድራል ውስኪ። እዛው ትናንትና አንቺን ከማይበት ከጠፍጣፉ ድንጋይ ተቀምጬ እያለሁ አንዱ አብሮ አደጌ በመኺና ባ…

9d ago👁 3.7Kopen

ለፀሐይ ፍካት ማን ይፈግጋል? ለሰማይ ንጣት ማን ይደግሳል? ማን ግድ ብሎት ማን ስሜት ሰጥቶት? ከምድር አልፎ ሰማዩን አይቶት?¡ ዘልቋል ከውስጥኽ?ገብቶሃል ቅኔው? ምን ብትነጠፍ ሰማይ ብትሆነው የያዘው እክል እስካልለቀቀው፧ ከኑሮ አሻግሮ ግትር አንገቱን እስካላዞረው፧ መቼም አያይህ ያልቀናለት ሰው! By @alem3_b [ዓለም] @getem @getem @getem

9d ago👁 3.7Kopen

ይቅር በላቸው [ፀሎት] የሞገቱኝን ሽራፊ ቀኖች ያስጀነኑኝን ጎዶሎ ሀብቶች... _ _ _ ሸንበቆ ድግፍ እፍኝ ትምክህቶች መውደቂያ ያጡ ድፍን ተምኔቶች! ይቅር በላቸው... የተጣደፉ ፈራጅ ከንፈሮች ያልተማከሩ ልብና አፎች! ያልደነገጡ ድንድን ስሜቶች ያልተረጋጉ ሰንካላ እምነቶች! ይቅር በላቸው! ይበልጥም ... የሞገቱኝን ሽራፊ ቀኖች! ያስጀነኑኝን ጎዶሎ ሃብቶች! _ _ _ ያስመከቱኝን ውዥቅ ቀለማት ያስፎከሩኝን ግንጥል ድምቀታት! ይቅር በላቸው! አልደበቁኝም ልሽሽው ካልኩት አላስጣሉኝም ከተሯሯጥኩት አላወጡኝም ከሰው ትከሻ ወይ አልሰጡኝም ዝና ሙገሳ፨ ይቅር በላቸው! ማራቸው ያለህ ልቤ አስታኮ፧ አብረህ አስበኝ ሊልህ ነው እኮ፧፧…

10d ago👁 4.4Kopen

እንዳትመለሺ ፣ መምጪያ መንገድሽ ላይ እሾህ ብዘራበት ... ልቤ ሳቅ ታየበት ... የጨለመው ዓይኔ – ብርሃን ዘነበበት ኃጢያትም አንዳንዴ – የእግዜር እጅ አለበት By Thomas Atsede @getem @getem @paappii

12d ago👁 2.3Kopen

የቁም ፍቅር ስደክም ብውል አዳር ብለፋም፤ አስታውሳለሁ ከውስጤ አይጠፋም፤ የዛ ቀን ግለት የዛች ቀኑ ፍም፤ ያገኘሁሽ ቀን በዛች ካፌ ፍክት ብለሽ፣ ያየሁሽ ለታ እዚያ ጥግ ላይ ስልክሽን ይዘሽ፤ 'ሰው አለው' ብዬ ወንበሩን ልስብ፣ ገና ሳልለው እንዲሁ ባሳብ፤ ሳወጣ ሳወርድ ቃላት ስመርጥ፣ አይንሽን ስቃኝ ከንፈሬን ስመጥ፤ እንዲሁ ቆሜ እንዲሁ እንዳለሁ፤ ለካ ሳላውቀው እረዥም ሰአት ተገትሬያለሁ፤ አሁን ስመለስ ራሴን ሳገኘው፤ ዙሪያ ገባውን ባይኔ ብቃኘው፤ አልለማ አልሰማ አልጠፋ አልበራ፤ እንዲሁ ብቻ ግትር ብዬ እንደጅብራ፤ 'እብድ ነው?' በሚል አስተያየትሽ ብትገረምሚኝ፤ አቅፌው ሄድኩኝ ያንድ ደቂቃ ፍቅሬን ሳትሰሚኝ፤ By @La…

12d ago👁 3.4Kopen

የሰካራሙ ፍልስፍና ✍️ እዚያ ሰማይ ከማደሪያው ከመቅደሱ፣ ሱራፌል ተጋርዶ ፊቶቹን ይሰጋል እዚህ ምድር አንድ ሰካራም ሰው፣ ለእግዚያር ምክር ይዞ በድፍረት ያወጋል እንደዚህ ይለዋል በሰካራም ድምጡ በደልና መፅድቅ እንዲለዋወጡ... እንዲህ ተናገረ... " ሰማያት ያለኸው፣ እግዚያር ሆይ ጌታዬ ሃሳብ ቢጤ ላንተ፣ በፊትህ ከታዬ ምን መሰለህ እግዚያር... በዚህኛው አለም በምንኖርባት፣ ሰዎች በተቃርኖ መርህ ይኖራሉ ተው!...ስትል ጥሰው፣ አድርግ ያልካቸውን መቼ ያደርጋሉ? እኔንም ተመልከት... አትስከር ያልከውን፣ ትዛዝህን ልጥስ ዘውትር እየጠጣው፣ ዘውትር ለምን ላልቅስ? ስለዚህ እግዝያር ለዚህ ተቃርኖ ዛር አንድ መፍትሔ አለኝ...…

12d ago👁 2.9Kopen

"ቃል ያለ ቃል" ስንን ያለ ኮሳሳ ባለ ማወቅ የከሳ ስልል ያለ ስናና ተካድኖት ኦና ይቆማል አይቆምም ይገጥማል አይገጥምም ይጠራል አይጠራም ይጮኻል አይሰማም እንዲህ ነው... ቃል ያለ ቃል ነፍስ ያደርቃል። በአጀባ ያንቃል በሁካታ ይደቃል ለሞት ያነቃል ኮታ ይነጥቃል። ቃል ያለ ቃል ነፍስ ያደርቃል። By Natnael Abebe @getem @getem @paappii

12d ago👁 2.9Kopen

ሀገር እንደ ጭድ ኮስኩሳኝ ሳስታውሳት ስትረሳኝ ኢትዬጵያ ወባ ሆናብኝ ራሴ...ለአንገት ከብዳብኝ ሀገር ጀርባዋን ስታሳየኝ ስተን እንደ ሽታ ወገን ሚባል ጠፋኝ ረግፎ በበሽታ ሀገርማ ጫንቃዋማ ቆስሏል እንደ ንፍሮ ሀገርማ ፊቷማ ተቀባብቷል በፊልትሮ ህዝብ ሚሉት እየሰመጠ ጉድጓድ ደርሷል የግል ኑሮ ሀገር እንደ ጭድ ኮስኩሳኝ ሳስታውሳት ስትረሳኝ እያደርኩ እየሞትኩኝ ጥንብ አንሳ ላያነሳኝ ሰው መሆንጥሎኝ አውሬ ነው የሚያነሳኝ ብቻ ጭዱ ያለቦታዋ እኔን ማቀፍ ለምን ሻተች ሀገር ታጥባ ወታ በእኔ እቅፍ እየሸተተች ለመሽተቴ አትፍረዱ እንባዬ ነው የሚያወዛኝ ሳቅ ባክህ አይባልም ሀገር ሞቶበት ላለ ሀዛኝ ሀገር ወባ ሆና ስታንቀጠቅጠኝ በትኩ…

17d ago👁 2.7Kopen

"ይድነቅሽ ድንቄ" ይለቀማል ጥጥ ፣ ይለቀማል ወርቁ ግዮን መፍሰሻሽስ ፣ እግዚያር ነው ስንቁ ላለማለቁ! እንደወንዝሽ ያለ ፣ ሌላ ወንዝ አውቄ ጅረቱ ከእሳት ፣ መፍሰሱ ለጽድቄ ገረመኝ ደነቀኝ ፣ ይድነቅሽ ድንቄ ጠጥቼው መጣሁ ፣ ልነግርሽ ፈልጌ ከምንጩ ስጠጣ ፣ታወቀኝ መፍለቄ እስከመጨረሻ ፣ ላይጠማኝ መጽደቄ By Natnael Abeba @getem @getem @getem

17d ago👁 2.5Kopen

channel description

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch @shiyach_bicha ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1

channel info

Telegram ID1148157627
Indexed sinceJun 4, 2026
Last refreshedJul 20, 2026

similar channels/art

support
@getem — ግጥም ብቻ 📘 · Telegram channel 64.2K subscribers · tgden