AI-саммари
Tikvah-University provides educational content and resources.
для кого: This channel is for individuals seeking educational materials and discussions on various topics.
графики · динамика
📨 Последние посты
97 всегоየኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የስቴም ማዕከል STEMpreneurship የክረምት መርሐግብር አስጀምሯል። 99 የተመረጡ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ፕሮጀክት መሠረት ባደረገው የክረምት መርሐግብር ይሳተፋሉ። መርሐግብሩ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የስቴም ማዕከል፣ STEMpower ኢትዮጵያ እና በአሜሪካው Case Western Reserve University በጋራ የተዘጋጀ ነው። ፕሮግራሙ በሦስት ልዩ ስልጠና ክፍሎች ማለትም ኬሚካል ማይክሮፋክተሪ፣ ኤሌክትሮኒክና ሮቦቲክስ እንዲሁም ሶፍትዌር ልማትና ዲጂታል ፈጠራ ተከፎሎ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል። @tikvahuniversity
በአዲስ አበባ በሚገኙ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩና በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ ደረጃ ለመሸጋገር ለተመዘገቡ መምህራን በበይነ መረብ የመግቢያ ፈተና ተሰጥቷል። በ2018 ዓ.ም የክረምት መርሐግብር 888 የአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ መምህራን የዲግሪ ትምህርት ለመማር መመዝገባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አሊ ከማል ገልፀዋል። ትምህርት ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰጠው ኮታ መሰረት 162 ለአንደኛ ደረጃ እንዲሁም 401 ለሁለተኛ ደረጃ በድምሩ 563 መምህራን በሚመደቡባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲግሪ ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ ተገልጿል…
#ጥቆማ አዲስ ሠልጣኞችን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክ አካዳሚ አሳውቋል። በኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (ESL) ስር የሚገኘው የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ፣ አዳዲስ ሠልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችለውን የትምህርት እና የመሠረተ ልማት ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቁን ገልጿል። አካዳሚው ዘመናዊ የማስተማሪያ መሠረተ ልማት፣ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ ካሪኩለሞች እና ብቁ የማስተማር አቅም በማሟላት ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጁ መሆኑን የአካዳሚው ዲን ሲራጅ አብዱላሂ ገልፀዋል። ሲሙሌተሮች በመጠቀም እና በባቦጋያ ሐይቅ ላይ በሚካሄዱ የተግባር ስልጠናዎች በከፍተኛ የደህንነ…
#LorcanMedicalCollege ሎርካን የሕክምና ኮሌጅ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በዲፕሎማ ያስተማራቸውን 122 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል። 17 ቱ በመደበኛ የትምህርት መርሐግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ የጥርስ ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን ሲሆኑ፤ ባለፈው ወር የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ወስደው ሙሉ በሙሉ ያለፉ ናቸው። ቀሪዎቹ 105 ተመራቂዎች በዲፕሎማ ፕሮግራም በክሊኒካል ነርሲንግ፣ በፋርማሲ እና በጥርስ ቴራፒ የሙያ መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል። @tikvahuniversity
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በክረምት የትምህርት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ ደረጃቸውን ለሚያሻሽሉ 611 መምህራን የመግቢያ ፈተና በበይነ መረብ ተሠጥቷል። የመግቢያ ፈተናው በክልሉ ሦስቱም ዞኖች፣ በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ እንዲሁም በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የሚያስተምሩ የዲፕሎማ መምህራንን ያጠቃልል መሆኑ ተገልጿል። የክረምት የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ፕሮግራም ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ መቆየቱና ዘንድሮ እንዲሠጥ በትምህርት ሚኒስቴር መፈቀዱ ይታወቃል። @tikvahuniversity
🔔 እስከ ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ የ 30% ቅናሽ አድርገናል! በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለም፣ ዘመኑ ያፈራቸውን የላብራቶሪና የስቱዲዮ እቃዎችን በማሟላት በሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ! ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች! 🎯 Graphics Design 🎯 Video Editing 🎯 Digital…
#FTTI የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴል እና ቱሪዝም ማኔጅመንት የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 350 ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል። የኢንስቲትዩቱ 58ኛ ዙር ተመራቂዎቹ በዲግሪ እና በደረጃ ፕሮግራሞች ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው። @tikvahuniversity
#ጥቆማ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት (AAU-MCS) በማቋቋም በ2019 ዓ.ም ከ1ኛ-7ኛ ክፍል ለማስተማር ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። በመሆኑም ልጆቻችሁን በሚከፈተው የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ማስመዝገብ የምትፈልጉ ወላጆች የሚከተሉትን መረጃዎች ልታውቁ ይገባል፦ የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 14-21/2018 ዓ.ም የምዝገባ ቦታ 5 ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና ቢዩልት ኢንቫይሮንመንት ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር E04 ትምህርት ቤቱ የሚገኝበት ቦታ፦ 5 ኪሎ (በቀድሞው የድኅረ ምረቃ/ፋርማሲ ትምህርት ቤት ግቢ) የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 1,000 ሲሆን፤ በቀጣይ ወርሃዊ የክፍያ መ…
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 1,569 መምህራን መንግሥት ባመቻቸው የክረምት ትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የመግቢያ ፈተና በዛሬው ዕለት ወስደዋል። የመግቢያ ፈተናው በ13 ማዕከላት በበይነ መረብ መሠጠቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አስከብር ወልዴ ገልፀዋል። 1,569 የመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን፣ ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ የትምህርት ደረጃቸውን ለማሻሻል እንዲችሉ በ10 የትምህርት አይነት የተሰጠውን የመግቢያ ፈተና ወስደዋል። የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ መመህራን የትምህርት ሚኒስቴር ባመቻቸው ነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ በመሆን በክረምት መርሐግብር ዩኒቨርሲቲ ገብተው እንደሚማሩ ተ…
11ኛ ዙር የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) ስልጠና የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም ይጀመራል። 👉 AutoCAD, Revit, እና 3D Max ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ 👉 ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕ የሚሰጥ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute Ti…
ነጻ የስልጠና ዕድል ጥቆማ የኢፌዴሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በ STEM Summer Program የተለያዩ ስልጠናዎች ለመስጠት ምዝገባ እያደረገ ነው፡፡ በቀሩት ጥቂት ቀናት ምዝገባዎን ያድርጉ! የስልጠና መስኮች፦ ● Coding ● Graphic Design, Multimedia & Video Production ● Digital Marketing, Content Creation & Entrepreneurship ● Electrical, Electronics & Embedded Systems ● Robotics, Automation & Intelligent Systems ● Technical Drawing & Woodworking ● CAD Design, SolidW…
#ጥቆማ የኢፌዴሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በተለያዩ መስኮች የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች ለመስጠት ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን ገልጿል። በከተማ ሆርቲካልቸር መስክ በቅርብ ቀን ስልጠና መሰጠት እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡ የከተማ ሆርቲካልቸር መስክ ስልጠናው ሰልጣኞች የተግባር እና የሥራ ፈጠራ ክህሎቶች የሚያገኙበት ነው ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity
о канале
похожие каналы/education
Telegram Tips
Telegram Tips provides information and guidance on utilizing Telegram's features for enhanced privacy and usability.
Дайте TON!
A Telegram channel providing analysis, insights, and opinions related to the TON blockchain.
Maths By Gagan Pratap
Maths By Gagan Pratap provides resources to help individuals prepare for government exams.
Maths By Aditya Ranjan - (Vidyagram) 🇮🇳
Maths By Aditya Ranjan - (Vidyagram) 🇮🇳 provides educational content and resources for mathematics learners.
рост бесконечным не будет
A personal diary sharing reflections and experiences.
Tips de Telegram
This channel provides tips and information about Telegram's features, focusing on ease of use and privacy.
