T
TIKVAH-ETHIOPIA
/tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA

Открыть в Telegram  →

AI-саммари

TIKVAH-ETHIOPIA is a Telegram channel for the Tikvah (Hope) Ethiopia family, serving as a platform for information and communication.

для кого: This channel is for members of the Tikvah Ethiopia community seeking information, updates, and a space for communication

1.6Mподписчики
206.5Kохват
13.0%ER
1.4постов/день

графики · динамика

1.58M
0(0.00%)
2 июл. – 20 июл. · 6

📨 Последние посты

95 всего

#WorldCup : ስፔን የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ሆነች። በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ከአርጀንቲና ጋር የተፋለመችው ስፔን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫው ባለቤት ሆናለች። የጨዋታው መደበኛው 90 ደቂቃ አልቆ በተጨማሪው 30 ደቂቃ ላይ ነው አንድ ጎል አስቆጥራ ያሸነፈችው። በሙሉ ጨዋታው ስፔን ከፍተኛ ብልጫ ወስዳ ነበር። ሊዮኔል ሜሲ ተከታታይ የዓለም ዋንጫ የሚያሳካበት እድል ሳይሰምር ቀርቷል። ቲክቫህ ስፖርት ሃምሌ 13 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia @tikvahethsport

1 дн. назад👁 119Kоткрыть

" ... ለውጭ አገር ባለሀብቶች የሚሰጥና እስከ 10 ዓመት የሚያገለግል ‘ጎልደን ቪዛ’ ካርድ በያዝነው በጀት ዓመት ወደ ስራ ይገባል " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት (ለቲክቫህ ኢትዮጵያ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት (ICS) ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለሚያበረክቱ የውጭ አገር ባለሀብቶች የሚሰጥና እስከ 10 ዓመት የሚያገለግለው ‘ጎልደን ቪዛ’ ካርድ በያዝነው የ2019 በጀት ዓመት ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚያደርግ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ይህ ‘ጎልደን ቪዛ’ ተብሎ የተሰየመው የመኖሪያ ፈቃድ እንደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) ባሉ እና በሌሎችም ሃገራት በካርድ መልክ የሚሰጥና ለውጭ ባለሀብቶች/…

2 дн. назад👁 181Kоткрыть

የስኬት ባንክ መረብ ኳስ ቡድን የ2018 ዓ.ም የኢሠማኮ አገር አቀፍ የስፖርት ውድድር ሻምፒዮን ሆነ 🏆 🏐 🎉 በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አዘጋጅነት በአገር አቀፍ ደረጃ በታላቅ ድምቀት ሲካሄድ የሰነበተው የ2018 ዓ.ም የኢሠማኮ የስፖርት ውድድር ላይ ሲሳተፍ የነበረው የስኬት ባንክ የወንዶች መረብ ኳስ ቡድን ሻምፒዮን ሆነ። እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን! ስኬት ባንክ የስኬትዎ መሰረት!

2 дн. назад👁 163Kоткрыть

የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶችን የአንድ ጊዜ የስራ ዘመን 6 ዓመት እንዲሆን የሚያዝ መመሪያ አውጥቷል። 👉 በመመሪያው ድንጋጌ መሰረት ለፕሬዝዳንትነትና የሚወዳደሩ ወንድ እጩዎች ቢያንስ የረዳት ፕሮፌሰርነትና ከዚያ በላይ የአካዳሚክ ማዕረግ ሊኖራቸው ይገባል። የየትምህርት ሚኒስቴር በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሾሙ ፕሬዝዳንቶችና ምክትል ፕሬዝዳንቶች አሰያየምን የሚገዛ አዲስ መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 1146/2018) ይፋ አድርጓል። ይህ መመሪያ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የነበረውን የአመራር አሰያየም ስርአት በመቀየር፣ በብቃትና በውድድር ላይ የተመሰረተ አሰራርን ለማስፈን ያለመ መሆኑን ይገልጻ…

2 дн. назад👁 261Kоткрыть

የሁለተኛው ሳምንት ሀሙስ በደቡብ አፍሪካ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፣ በየሳምንቱ ሐሙስ ከፀረ-ስደተኛ ቡድኖች ይደርስ የነበረው ጥቃትና ማሳደድ በዚህ ሳምንት ሁለተኛው ዙር እንደተሰጋው አለመሆኑንና ሁኔታው በአንጻራዊነት የተረጋጋ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ቀደም ሲል አክራሪ የፀረ-ስደተኛ ቡድን በየሳምንቱ ሐሙስ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች በራሱ ኃይል እየያዘ ለፖሊስ እንደሚያስረክብ ዝቶ ነበር። ይህን ተከትሎም ከሰኔ 30 (እ.ኤ.አ) በኋላ በነበረው የመጀመሪያ ሳምንት ሐሙስ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ከፍተኛ እንቅስቃሴ በመደረጉ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የው…

2 дн. назад👁 240Kоткрыть

#Zambia - ወደ ደቡብ አፍሪካ ህገወጥ በሆነ መንገድ ሊገቡ የነበሩ 9 ኢትዮጵያውያንን እና እነሱን በጭነት መኪና ሲያዘዋውሩ የነበሩ 2 የዚምባብዌ ሹፌሮች " ካዙንጉላ " የተባለ አካባቢ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዛምቢያ የኢሚግሬሽን መምሪያ አሳወቀ። ተጠርጣሪዎቹ በህገ-ወጥ ሰዎችን በማዘዋወር ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን፣ ዘጠኙ (9) ኢትዮጵያውያንም ህጋዊ ሂደታቸውን እየተጠባበቁ መሆኑ ተገልጿል። መምሪያው በድንበር አካባቢዎች የሚደረገውን ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሃምሌ 11 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

2 дн. назад👁 210Kоткрыть

#NationalDialogue 🇪🇹 ኮሚሽኑ ሁሉም የፓርቲ ተሳታፊዎች በአንድ አጀንዳ ብቻ እንዲሳተፉ የሚገድብ አካሄድ ላይ ጥያቄ ቀረበበት። የሀገራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ፓርቲ ተሳታፊዎች ለውይይት በቡድን የተደራጁበት አካሄድ ሁሉም የፓርቲ ተወካዮች በአንድ አጀንዳ ብቻ እንዲሳተፉ የሚያደርግ በመሆኑ፣ በተለያዩ አጀንዳዎች እንዲሳተፉ ለኮሚሽኑ ጥያቄ ቀርቧል። የኢዜማ ተወካይ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን፣ ከአንድ…

2 дн. назад👁 206Kоткрыть

" በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ሳይሰጥ ጋዜጠኞችንና ዋና አዘጋጆችን ለእስራት መዳረግ የተከለከለ ነው " - ወ/ሮ ስመኝ ውቤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የተዘጋጀው የመረጃ ነጻነት አዋጅ ቁጥር 1427/2018 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 18/2018 ዓ.ም. መጽደቁ ይታወቃል። በዚህ የመረጃ ነጻነት አዋጅ መሠረት፣ በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ለምርመራም ሆነ ለሌላ ምክንያት ጋዜጠኞችን፣ ዋና አዘጋጆችን እና ከጉዳዩ ጋር የተያያዘ ሌላ ሰው ለእስራት መዳረግ የተከለከለ መሆኑን ዋና ዕንባ ጠባቂዋ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ ገልጸዋል። ወ/ሮ ስመኝ አክለውም፣ መረጃን በቅን ልቦና ያሰራጨ…

3 дн. назад👁 244Kоткрыть

እንደልብ እንገናኝ! 💚 የቦታ፣ የጊዜ እና የኔትወርክ ገደብ ሳይከለክለን ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንደልብ እናውራ! የሳምንት በ30 ብር ብቻ 120 ደቂቃ በመግዛት ከሳፋሪኮም (07) ወደ ቴሌ (09) እንደልብ ይደውሉ። አሁኑኑ *777*1# ብለው ይደውሉ! #SafaricomEthiopia #VoicePackage

3 дн. назад👁 214Kоткрыть

በፍሊንትስቶንስ አ.ማ እና በ ደንበኞቹ መካከል 2 ዓመት በላይ ሲያከራክር የቆየው ጉዳይ በፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት መቋጫ አገኘ። 👉 በብያኔው መሰረት ፍሊንትስቶንስ አክስዮን ማህበር ለቀድሞ ደንበኞቹ ከ 282 ሚሊየን ብር በላይ የካሳ ክፍያ የሚከፍል ይሆናል። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቀን 08/11/18 ዓም በዋለው ችሎት፣ "ፍሊንትስቶንስ ኢንጅነሪንግ አ.ማ"(በአሁኑ ስያሜ ፍሊንትስቶንስ አ.ማ) ከድርጅቱ ቤት ገዝተው ግንባታ ርክክብ ባለማግኘታቸው ምክንያት ክስ የመሠረቱ 212 ደንበኞችን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በግልግል ዳኝነት ጉባኤ የተሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል። ጉዳዩ የተጀመረው ፍሊንትስቶንስ ኢንጅነሪንግ…

3 дн. назад👁 227Kоткрыть

#NationalDialogue 🇪🇹 " ለእኔ ሳይሆን ለእኛ፣ ለሰፈሬ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ማለት ከቻልን ይህ ምክክር ፍሬያማ ይሆናል " - ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) 👉 " ይህ ጉባኤ በቀላሉ የማይደገም ነው ! " በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ደጋግሞ የሚታየውንና በኃይለቃል ጀምሮ በኃይል እርምጃ የመደምደም የፖለቲካ ስብራት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማቆም ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)…

6 дн. назад👁 96.7Kоткрыть

#NationalDialogue 🇪🇹 ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄድ ጀምሯል፡፡ በምክክር ጉባኤው ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ 4 ሺህ ተመካካሪዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡ ቪድዮ ፦ AMN @tikvahethiopia

6 дн. назад👁 113Kоткрыть

описание канала

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። ማስታወቂያ፦ 📞 0979333111 @TikvahEthMarketingBot መረጃና መልዕክት ፦ 0998999899 ​@tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna

о канале

Telegram ID1130580549
В каталоге с17 мая 2026 г.
Обновлён20 июл. 2026 г.

похожие каналы/lifestyle

поддержка